ቅድስት ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን፡ እግዚአብሔር ልባቸውን ባነሳሳቸው ጥቂት ምዕመናን፡ በአውሮፕያውያን ቀን አቆጣጠር ጃንዋሪ 17, 1999 (January 17, 1999) ተመሰረተ።ለዚህም መነሻው: እንደ አጋጣሚ ሆኖ የ1998 የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አመታዊ ፒክኒክ: የፍልሰታ ጾም ፊቺ ጋር ስለተገጣጠመና: በአንዳንድ እናቶች: አገራችን ብንሆን ኖሮ ዛሬ አስቀድሰን ጾም እንፈታ ነበር ሲሉ: ሌሎችም ታዲያ ለምን እዚህ ቤተክርስቲያን አይኖረንም? የሚለው የተቀደሰ ሀሳብ ስለመጣላቸው: በተለያየ ጊዜና አካባቢ እየተገናኙ ሲወያዩ ቆይተው: የካቲተ 17, 1999 ላይ በነበረው ምልዐተ ጉባኤው ላይ: ለውይይት የቀረበውን ረቂቅ መተዳደሪያ ደንብና ኮድ ኦፍ ኤቲክስ አጽድቆ: ስሙንም ኪደነምህረት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ብሎ: ቀጥሎም የሚመሩትን የቦርድ አባላት መርጦ በደስታ ተበተነ።


የአገልግሎት ቅጾች

መልክቶች

ይርዱ

ማስታወቂያ

ፎቶ ጋለሪ

      ዓመታዊ ንግስ  በሮቸስተር ኪዳነምህረት

 የኢ .ኦ. ተ ቤተክርስቲያን

የ2023 መስቀል በዓል አከባበር🟢🟡🔴

የብፁዕ  አቡነ ባስልዮስ ጸሎተ ፍትሃት እና ሽኝት

ቅዱሳን አባቶች  ከ1951  - እስካሁን

    ግብጽ ቤተ ክርስቲያን ጋር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አመራር ላይ ብዙ ጊዜ የወሰደ ድርድር ከተደረገ በኋላ ስምምነት ተደርጎ፥ እሑድሰኔ ፩ ቀን ፲፱፻፶፩ ዓ/ም፤ ንጉሠ ነገሥቱም በተገኙበት ሥነ-ሥርዓት ፓፓው አቡነ ቄርሎስ ፮ኛ በብፁዕ አቡነ ባስልዮስ ላይ የሢመቱን ሥርዓተ-ጸሎት አድርሰው፤ የፓትርያርክነቱን ዘውድ ባርከው ደፉላቸው። ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ አቡነ ባስልዮስ በግብጽ ፓትርያርክ እጅ በዚህ ማዕርግ ሲቀቡ የመጀመሪያውም የመጨረሻውም ኢትዮጵያዊ መሆናቸው ነው። 

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ  ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ  አቡነ ባስልዮስ  ፲፱፻፶፩-፲፱፻፷፫

 ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት

 ዘኢትዮጵያ  አቡነ ቴዌፍሎስ

፲፱፻፷፫ - ፲፱፻፷፰

 ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት 

ዘኢትዮጵያ አቡነ ተክለሃይማኖት

፲፱፻፷፰ -፲፱፻፹ 

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት 

ዘኢትዮጵያ አቡነ መርቆሬዎስ

፲፱፻፹ - ፳፻፲፬

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ

 ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ 

ዘአኵስም ወዕጨጌ  ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

፲፱፻፹፬ - ፳፻፭ 

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ

 ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ 

ዘአኵስም ወዕጨጌ   ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

፳፻፭ - እስካአሁን