ሥርዓተ አምልኮ ክፍል አንድ

ርዓት  “ሠርዐ” ሠራ ከሚለው የግእዝ ቃል የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ደንብ፣ አሠራር፣ መርሐ ግብር ማለት ነው። በሃይማኖት ውስጥ የሚፈጸም የመንፈሳዊ አገልግሎትና አሠራር እንዲሁም ክርስቲያናዊ ሥርዓትን ያመለክታል።

 ሥርዓተ አምልኮት

የቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ አምልኮት ለአምላካችን እግዚአብሔር የሚቀርብ ሥርዓት ነው፡፡ ይህም ሥርዓተ ጸሎትን፣ ሥርዓተ ጾምን፣ ሥርዓተ ምጽዋት፣ ሥርዓተ ስግደትን፣ ሥርዓተ በዓላትን፣ ሥዕላትን፣ መስቀልንና ንዋያተ ቅድሳትን ያካትታል


ሥርዓተ አምልኮ


ሥርዓት  “ሠርዐ” ሠራ ከሚለው የግእዝ ቃል የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ደንብ፣ አሠራር፣ መርሐ ግብር ማለት ነው። በሃይማኖት ውስጥ የሚፈጸም የመንፈሳዊ አገልግሎትና አሠራር እንዲሁም ክርስቲያናዊ ሥርዓትን ያመለክታል።

 ሥርዓተ አምልኮት

የቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ አምልኮት ለአምላካችን እግዚአብሔር የሚቀርብ ሥርዓት ነው፡፡ ይህም ሥርዓተ ጸሎትን፣ ሥርዓተ ጾምን፣ ሥርዓተ ምጽዋት፣ ሥርዓተ ስግደትን፣ ሥርዓተ በዓላትን፣ ሥዕላትን፣ መስቀልንና ንዋያተ ቅድሳትን ያካትታል፡፡

፩. ሥርዓተ ጸሎት

ጸሎት ቃሉ ግእዝ ሲሆን “ጸለየ፣ ለመነ” ከሚለው ግሥ የወጣ ነው፡፡ የቃሉ ትርጉምም ልመና እንዲሁም ምስጋናም ነው፡፡ ለምሳሌ “ይትቀደስ ስምከ” /ስምህ ይቀደስ/ ስንል ምስጋና ነው፡፡ “ሲሳየነ ዘለለዕለትነ ሀበነ ዮም” (የዕለት ምግባችንን ዛሬ ስጠን) ስንል ደግሞ ልመና ነው፡፡ እንዲሁም ጸሎት ሰው ከልዑል እግዚአብሔር ጋር የሚነጋገርበት ነው፡፡ (ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ ፲፬)

ሀ. ሰባቱ የጸሎት ጊዜያት

ነቢዩ ዳዊት “ስለ ጽድቅህ ፍርድ በቀን ሰባት ጊዜ አመሰግንሃለው” ብሎ እንደተናገረ በቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ሰባት የጸሎት ጊዜያት አሉ፡፡ (መዝ.፻፲፰-፻፷፬)

ጸሎተ ነግህ

ነቢዩ ዳዊት “አምላኬ አምላኬ በማለዳ ወደ አንተ እገሰግሳለሁ” በማለት እንደተናገረው ሌሊቱ አልፎ ቀኑ ሲተካ ከጥዋቱ በዐሥራ ሁለት ሰዓት የምንጸልየው የጸሎት ዓይነት ነው፡፡ (መዝ.፷፪÷፲፩)

በነግህ የምንጸልየው፡-

፩. በዚህ የጸሎት ጊዜም ሌሊቱን በሰላም ስላደረሰን አምላካችን እግዚአብሔርን እናመሰግናለን፡፡ ዕለቱንም ከክፋት እንዲሠውረን፣ ከፈተና እንዲያወጣን እና በሰላም እንዲያውለን እንጸልያለን፡፡

እግዚአብሔር አምላክ አዳምን የፈጠረው በነግህ በመሆኑ ያንን ታሳቢ በማድረግ  እንጸልያለን፡፡

፪. ቅዱሳን መላእክትም ለተልእኮ ሲፋጠኑ የሚገናኙበት ሰዓት በመሆኑ የእነርሱን አማላጅነትና ተራዳኢነት በመታመን እንዲሁም የሌሊቱ ጠባቂ መልአክ ተልእኮውን ጨርሶ በቀን በሚጠብቀን መልአክ የሚተካበት እንደመሆኑ ሁለቱ ጠባቂ መላእክት የሚገናኙበት ሰዓት በማሰብ በዚህም ሰዓት እንጸልያለን፡፡

፫. ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሰው ልጆች በደል በጲላጦስ ዐደባባይ የቆመበት ሰዓት በመሆኑም እንጸልያለን።

ጸሎተ ሠለስት

ይህ የጸሎት ሰዓት በሦስት ሰዓት የሚጸለይ ነው፡፡

በሦስት ሰዓት የምንጸልየው፡-

፩. እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የቅዱስ ገብርኤልን ብሥራት የሰማችበት በመሆኑ

፪. ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሰው ልጆች ሲል በጲላጦስ አደባባይ የተገረፈበት ሰዓት ስለሆነ

፫. ነቢዩ ዳንኤል ፊቱን ወደ ኢየሩሳሌም አቅጣጫ መልሶና የቤቱን መስኮት ከፍቶ የጸለየበት ሰዓት በመሆኑ

፬. ለአባቶቻችን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ የወረደበት /በኢየሩሳሌም ጸንተው በመቆየታቸው ከእግዚአብሔር ዘንድ ይህንን ታላቅ ጸጋ የተቀበሉበት /ሰዓት ነው፡፡

ቀትር

የቀትር ሰዓት የሚጸለየው በዕለተ እኩሌታ (በስድስት ሰዓት) ላይ ነው፡፡ በዚህ ሰዓትም የምንጸልየው በሚከተሉት ምክንያቶች ነው፡፡

፩. አዳም በጥንተ ጠላት ዲያብሎስ ተታሎ ዕፀ በለስን  በመብላቱ ከክብሩ የተዋረደበት ስለሆነ ያን በማስታወስ እንጸልያለን፡፡

፪. አዳም ዕፀ በለስን በልቶ የሞት ፍርድ ስለተፈረደበት ኃጢአተ በደሉን ሊያጠፋለት ሲል ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቀራንዮ ዐደባባይ የተሰቀለበት በመሆኑ

፫. ቀትር የቀን እኩሌታ በመሆኑ የፀሐይ ሙቀት የሚያይልበትና የሰው ልጅ ለድካም የሚዳረግበት በመሆኑ አጋንንት ስለሚበረቱበት በቀትር ሰዓት እንጸልያለን፡፡

ተሰዓተ ሰዓት

በዚህ የጸሎት ጊዜ (በዘጠኝ ሰዓት ላይ) ዐራተኛውን ጸሎት እናደርሳለን። ጸሎት የምናደርግበት ምክንያቶችም የሚከተሉት ናቸው፡፡

፩. ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ መከራ ሥቃይን ተቀብሎ ቅዱስ ሥጋውን ከቅድስት ነፍሱ የለየበት ሰዓት ነው።

፪. ቅዱሳን መላእክት የሰው ልጆችን በጎም ሆነ ክፉ ሥራ ወደ ፈጣሪ የሚያሳርጉበት ነው፡፡

፫. በዚህ ጊዜ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መከራ እና ሞት አያሰብን ቅዱሳን መላእክት ከፈጣሪያቸው እንዲያስታርቁን እየለመንንና እየተማጸንን እንጸልያለን፡፡

ጸሎተ ሠርክ

የሠርክ ጸሎት ጊዜ በዐሥራ አንድ ሰዓት የሚጸለይ ጸሎት ነው፡፡ ቅዱስ ዳዊት እንዲህ ይላል፡፡ “ጸሎቴን እንደ ዕጣን በፊትህ ተቀበልልኝ እጅ መንሳቴም እንደ ሠርክ መሥዋዕት ትሁን” (መዝ.፻፵÷፪)

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለምን ለማዳን በፈቃዱ ነፍሱን ከሥጋው ከለየ በኋላ ወደ መቃብር የወረደበት ሰዓት ነው፡፡ (ማቴ.፳፯÷፶፯)

ጸሎተ ንዋም

ንዋም መኝታ ማለት ነው፤ ከምሽቱ ሦስት ሰዓት በሆነ ጊዜ ዕለቱን በሰላም አሳልፈን ለሌሊቱ ዕረፍት የምንዘጋጅበት በመሆኑ በሰላም ላዋለን ፈጣሪ በሰላም እንዲያሳድረን ከሌሊት አጋንንትና ከቅዠት እንዲጠብቀን እየተማጸንን እንጸልያለን፡፡

በዚህ ጊዜም የምንጸለየው፡-

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ ዛሙርቱን በጌቴሴማኒ ጸሎት ስላስተማራቸው እርሱ ስለጸሎት ማስተማሩን እያሰብን እንጸልያለን፡፡ 

መንፈቀ ሌሊት (እኩለ ሌሊት)

ቅዱስ ዳዊት ‘’መንፈቀ ሌሊት እትነሣእ ከመ እግነይ ለከ በእንተ ኵነኔ ጽድቅከ፤ ስለ ጽድቅህ ፍርድ በእኩለ ሌሊት አመሰግነህ ዘንድ እነሳለሁ” በማለት ይህ ሰዓት ከእግዚአብሔር ጋራ የሚነጋገርበት እንደሆነ ገልጿል፡፡ (መዝ.፻፲፰፥፷፪)

በመንፈቀ ሌሊት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተልሔም ዋሻ የተወለደበት በመሆኑ እንዲሁም ሞትን ድል አድርጎ በታላቅ ኃይልም የተነሣበት ሰዓት በሌሊት ያንን ታሳቢ በማድረግ ነው።

ከዚህ በተጨማሪ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግመኛ ለፍርድ ሚመጣበትም ሰዓት  በመሆኑ ለከፈልንን መሥዋዕት እያመሰገንን ምሕረትን ድኅነትን እንድናገኝ ተስፋ በማድረግ በመንፈቀ ሌሊት እንጸልያለን፡፡

ለ. ሥርዓተ ቅዳሴ

ቅዳሴ ምሥጋና ማለት ነው፤ ይኸውም ለፈጣሪያችን እግዚአብሔር የምናቀርበው ምስጋና ነው፡፡ ሥርዓተ ቅዳሴ ወይም የቅዳሴ ሥርዓት በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከጸሎት ሁሉ በላይ የሆነ፡፡ ለአምላካችን እግዚአብሔር የምናቀርበው ምስጋና ከሰማያውያን መላእክት የተጀመረ ነው፡፡

ቅዳሴንም የጀመሩትም ሰማያውያን መላእክት ናቸው፤ ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአባታችን ለአዳም ከልጅ ልጁ ተወልዶ እንደሚያድነው ቃል የገባለት አምላካዊ የተስፋ ቃል ሲፈጸም ቤተ ልሔም በምትባል የዳዊት ከተማ “ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ስምረቱ ለሰብእ” ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን፤ ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ እያሉ እንዳመሰገኑ በሉቃስ ወንጌል ላይ ተጽፎ እናገኛለን። (ሉቃ.፪፥፲፬)

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በጸሎተ ሐሙስ ለደቀ መዛሙርቱ ኅብስቱን አንሥቶ ባርኮ ፈትቶ  “እንካችሁ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው፤ ጽዋውንም ይዞ አክብሮ አመስግኖ ሁላችሁም ከእርሱ ጠጡ ስለ ብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው” በማለት የቅዱስ ቁርባንን ሥርዓት በሠጠን መሠረትም ቅዱስ ቁርባን በቅዳሴ ሥርዓት ውስጥ ይፈጸማል፡፡ (ማቴ. ፳፮፣ ፳፮፥፳፱  ማር፥ ፲፬፣ ፳፪፥፳፭)

የቅዳሴ ሥርዓት አገልግሎት በሚፈጸምበት ቦታ ቅዱሳን መላእክት እንደ ቅጠል ረግፈው፣ እንደ ሻሽ ተነጥፈው የሚያከብሩት፣ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም ኅብስቱን በጻሕል፣ ወይኑን በጽዋ በማቅረብ ኅብስቱ ሥጋ ወልደ እግዚአብሔር፤ ወይኑ ደመ ወልደ እግዚአብሔር የሚሆንበት ነው።

ቅዱሳን ሐዋርያት ይህንን ሥርዓት ተረክበው ለትውልድ ትውልድ በማስተላለፋቸው ሥርዓቱ ሳይቋረጥ በቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዘወትር ይፈጻማል፡፡

በቅዳሴ ሥርዓት ወቅትም ለዕለቱ በተመደቡ ካህናትና ምእመናን በአንድነት በመሆን ለአምላካችን ምስጋና እናቀርባለን፤ ለበደላችን ይቅርታና ምሕረት እንጠይቃለን፤ ለኃጢአት ሥርየትን እናገኛለን፤ ሥጋ ወደሙ የበቃንም ቅዱስ ቁርባንን እንቀበላለን፡፡ በዚያም የዘለዓለም ሕይወትን እናገኛለን።


ሥርዓተ አምልኮ -ክፍል ሁለት

ሥርዓተ ጾም

ጾም

ጾም ‹‹ጾመ›› ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ቃል ሲሆን የቃሉ ፍቺም ‹‹መተው፣ መከልከል፣ መጠበቅ›› ማለት ነው፡፡ ጾም ለተወሠነ ጊዜና ሰዓት ሥጋችን ከሚፈልጋቸው መብል፣ መጠጥ እንዲሁም ማንኛውም ሥጋዊ ፍላጎት መከልከልና መወሰን ነው፡፡ በቤተ ክርስቲያናችን አስትምህሮ ‹‹ጾም በታወቀው ዕለት በታወቀው ሰዓት ሰው ከምግብ የሚከለከለው መከልከል›› እንደሆነ እንማራለን፡፡ (ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ ፲፥፲፭)

በክርስቲያናዊ ሕይወታችን ውስጥ ጾም ለአምላካችን እግዚአብሔር ፍቅር ስንል ሥጋችንን ለርኃብና ለጥማት አሳለፈን በመስጠትና በመትጋት የምንኖረው በመሆኑ የአምልኮት መገለጫ ነው፡፡ ጠላት ዲያብሎስ ከሚያመጣብን ፈተናም ለማለፍ ይረዳናል፡፡ ነቢዩ ዳዊት ‹‹ለእግዚአብሔር በፍርሃት ተገዙ››  በማለት እንደተናገረው ለአምላካችን እግዚአብሔር መገዛታችንን አምልኮታችንን ከምንገልጽባቸው ክርስቲያናዊ ተግባራት መካከል አንዱ ጾም ነው፡፡ (መዝ.፪፥፲፩)

ሥርዓተ አምልኮ

ክፍል ሁለት

ታኅሣሥ ፳፤ ፳፻፲፭ ዓመተ ምሕረት

ሥርዓተ ጾም

ጾም

ጾም ‹‹ጾመ›› ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ቃል ሲሆን የቃሉ ፍቺም ‹‹መተው፣ መከልከል፣ መጠበቅ›› ማለት ነው፡፡ ጾም ለተወሠነ ጊዜና ሰዓት ሥጋችን ከሚፈልጋቸው መብል፣ መጠጥ እንዲሁም ማንኛውም ሥጋዊ ፍላጎት መከልከልና መወሰን ነው፡፡ በቤተ ክርስቲያናችን አስትምህሮ ‹‹ጾም በታወቀው ዕለት በታወቀው ሰዓት ሰው ከምግብ የሚከለከለው መከልከል›› እንደሆነ እንማራለን፡፡ (ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ ፲፥፲፭)

በክርስቲያናዊ ሕይወታችን ውስጥ ጾም ለአምላካችን እግዚአብሔር ፍቅር ስንል ሥጋችንን ለርኃብና ለጥማት አሳለፈን በመስጠትና በመትጋት የምንኖረው በመሆኑ የአምልኮት መገለጫ ነው፡፡ ጠላት ዲያብሎስ ከሚያመጣብን ፈተናም ለማለፍ ይረዳናል፡፡ ነቢዩ ዳዊት ‹‹ለእግዚአብሔር በፍርሃት ተገዙ››  በማለት እንደተናገረው ለአምላካችን እግዚአብሔር መገዛታችንን አምልኮታችንን ከምንገልጽባቸው ክርስቲያናዊ ተግባራት መካከል አንዱ ጾም ነው፡፡ (መዝ.፪፥፲፩)

በመጽሐፈ ማር ይስሐቅ አንቀጽ ፬ ምዕራፍ ፮ ላይም እንደተለገጸው ‹‹ጾም ቁስለ ነፍስን የምትፈውስ፣ ኃይለ ፍትወትን የምታደክም፣ የበጎ ምግባራት ሁሉ መጀመሪያ ከእግዚአብሔር ወገን የምታሠጥ፣ የወንጌል ሥራ መጀመሪያ፣ ለጽሙዳን ክብራቸው፣ የድንግልና የንጽሕና ጌጣቸው፣ የንጽሕህና መገለጫ፣ የጸሎት ምክንያት እናት፣ የዕንባ መገኛ መፍለቂያዋ፣ አርምሞን የምታስተምር፣ ለበጎ ሥራ ሁሉ የምታነቃቃ፣ ሰውነትን በእግዚአብሔር ፊት በማዋረድ ትሕትናን ገንዘብ ለማድረግ የምትረዳ መድኃኒተ ነፍስ ናት፡፡››

በክርስቶትስ ክርስቲያን የተባልን ሰዎች በሙሉ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን የታወጁትን ሰባቱን አጸዋማትን ማለትም ‹‹ጾመ ነቢያትን፣ የነነዌ ጾምን፣ ዐቢይ ጾምን፣ ጾመ ድኅነትን (ረቡዕና ዓርብ)፣  ጾመ ሐዋርያትን፣ የገሃድ ጾምን  እና ጾመ ፍልሰታ ለማርያምን›› ጠንቅቆ በማወቅ ወቅቶቹንና ሥርዓቱን ጠብቀን ልንጾም ይገባል፡፡

የጾም ሥርዓት

በአጽዋማት ወቅት ልንጠብቃቸው የሚገባን ሥርዓቶች የክርስቲያናዊ ምግባራችን መገለጫዎች ናቸው፡፡ ይህም የጸሎት ሰዓታትን ጠብቆ ከመጸለይ በተጨማሪ በቤተ ክርስቲያን በመገኘት ጸሎት ማድረስ፣ ቅዳሴ ማስቀደስና ቅዱስ ቁርባንን መቀበል ናቸው፡፡ በእርግጥ እነዚህን ተግባራት በሌሎች ወቅቶችም ልንተገብራቸው ቢገባም በጾም ወቅት ግን ጾማችን በእግዚአብሔር አንድ ይታሰብልንና ተቀባይነት ያገኝ ዘንድ ከጾማችን ጋር እነዚህን ተግባራት ልንፈጽማቸው ይገባል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በአጽዋማት ወቅት ከጾሎታችን ጋር አብዝተን መስገድና መመጽወት ይገባናል፡፡

በጸሎትና በስግደት እንዲሁም በምጽዋት የታገዘ ጾም በእግዚአብሔር ፊት የተወደደ በመሆኑ ድኅነትን ማሰጠት ብቻም ሳይሆን በረከትን ያስገኛል፡፡ በዚህም የተነሣ ሥራችን፣ ትዳራችን እንዲሁም አገልግሎታችን ይባረክልናል፡፡

ሥርዓተ ምጽዋት

ምጽዋት ሥርወ ቃሉ የግእዝ ቋንቋ ሲሆን ትርጓሜውም ‹‹ስጦታ፣ችሮታ፣መለገስ›› ማለት ነው፡፡

ለተቸገሩ ሰዎች የምናደርገው ማንኛውም የገንዝብም ሆነ ቁሳዊ ርዳትን መመጽወት ይባላል፡፡ ይህም በተለይ የሚበሉትና የሚለብሱት ላጡ ነዳያን የሚደረግ ችሮታን ያመለክታል፡፡  በፍትሐ ነገሥት ፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ ፲፮ ቊ ፻፳፭-፻፳፯ እንደተገለጸው ‹‹ምጽዋት ምሕረት ነው፡፡ እግዚአብሔር ከሰጪዎች ጋር የሚሰጥ፣ ከተቀባዮች ጋር ሁኖ የሚቀበል፣ በመስጠትና በመቀበል በሰዎች መካከል መተሳሰብና መረዳዳት እንዲኖር ሀብትን ለሀብታሞች የሚሰጠው ከእነርሱ የሚያንሱትን እንዲያስተናግዱበት ነው፡፡››

ጠቢቡ ሰሎሞንም ‹‹ለደሀ ቸርነትን የሚያደርግ ለእግዚአብሔር ያበድራል፤ በጎነቱንም መልሶ ይከፍለዋል›› በማለት እንደተናገረው ምጽዋትን ለተቸገረ ሰው የሚሰጥ ለእግዚአብሔር መስጠት ነው፡፡ (ምሳ.፲፱፥፲፯)

ልዑል እግዚአብሔርም ከመሥዋዕት ይልቅ ምጽዋትን አብልጦ እንደሚወድ ተናግሯል፡፡ ‹‹እኔ የመረጠሁት ጾም …እንጀራህን ለተራበ ትቆርስ ዘንድ ስደተኞች ደሆችን ወደ ቤትህ ታገባ ዘንድ የተራቆተውን ብታይ ታስበው ዘንድ አይደለምን?›› እንዲል፤ (ኢሳ.፶፯፥፯)

መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ሲያስተምርም ‹‹ሁለት ልብስ ያለው ሰው ለሌላው ያካፍል፤ ምግብም ያለው እንዲሁ ያድርግ›› ብሏል:: (ሉቃ.፫፥፲፩)

ቅዱስ ዮሐንስ እንዳስተማረን በእግዚአብሔር ፊት ምጽዋትን እናደርግ ዘንድ በዕለት ከዕለት ከምናገኘው መብልና መጠጥ እንዲሁም አልበሳት ግምሹን ማካፈል ይጠበቅብናል፡፡ ሁለት እንጀራ ካለን አንዱን ለሌለው መስጠት እንዲሁም ትርፍ ልብስ ካለን በተመሳሳይ መልኩ ልብስ ለሌለው ማልበስ እንዳለብን መረዳት ያስፈልጋል፡፡ በዚህም ምግባራችን አምላካችን ደስ ይሰኛልና ለእርሱ ምጽዋትን እያቀረብን በአምልኮተ እግዚአብሔር እስከ ሕልፈተ ሕይወታችን ኖረን ርስተ መንግሥተ ሰማያትን እንወርሳለን፡፡

ሥርዓተ ስግደት

ስግደት ማለት ‹‹ማጎንበስ፣ መንበርከክ፣ በግንባር መውደቅ፣ ግንባርን ምድርን አስንክቶ መሬት ስሞ መመለስ›› ማለት ነው።

ስግደት ሁለት ዓይነት ናቸው፡፡ እነርሱም የአምልኮት ስግደትና የጸጋ ስግደት (ለእመቤታቸን ቅድስት ድንግል ማርያም የሚሰገድ ስግደት እንዲሁም ለቅዱሳን መላእክት፣ ለጻድቃንና ለሰማዕታተ የሚሰገድ ስግደት ናቸው፡፡ ነገር ግን በዚህ ርእሰ ጉዳያችን ላይ የምናየውና ከሥርዓተ አምልኮ ጋር የምንማረው ስለ የአምልኮተ ስግደተ ነው፡፡

የአምልኮት ስግደት

ለአምላካችን እግዚአብሔር የሚሰገድ ስግደት የአምልኮት ስግደተ ነው፡፡  በሉቃስ ወንጌል  ‹‹ለጌታ ለአምላክህ ስገድ፤ እርሱንም ብቻ አምልክ›› ተብሎ እንደተጻፈው በአርአያውና በአምሳሉ ለፈጠረን ፈጣሪያችን ስግደት እናቀርባናለን፡፡ (ሉቃ.፬፥፰)

ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም ‹‹ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አንዲት ስግደት እሰግዳለው›› እያልን ለአምላካችን እንድሰግድ ታስተምረናለች፡፡ ሰዎች ሰማያውያን መላእክትን ምሳሌ በማድረግ በፍርሃትና አክብሮት ለአምላካችን እንሰግዳለን፡፡

የአምላኮተ ስግደት ሥርዓት

ለልዑል እግዚአብሔር የሚሰገድ ስግደት በንጹሑ ስፍራና በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከቅዱስ ሥዕሉ ፊት የሚደረግ ነው፡፡ በምንሰግድበት ጊዜም ኅሊናችን ከክፋት ሁሉ ነጻ አድረገን በንጹሕ ልቡናና በፍርሃት ሆነን ግንባራችንን መሬት በማስነካት ልንሰግድ ይገባል፡፡

በምንሰግድበት ጊዜም ‹‹ለአብ እሰግዳለሁ፣ ለወልድ እሰግዳለሁ፣ ለመንፈስ ቅዱስ እሰግዳለሁ፣ ለአብ ምስጋና ይሁን፤ ለወልድ ምስጋና ይሁን፤ ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይሁን፤  በረከት ለሰጠኸን፣ እስኪዘህ ሰዓት ላደረስከን፣ በቸርነትህ ላኖርከን፣ በብርሀንህ ኃይል ለመራኸን ላንተ ክብር ምስጋና ይግባል፡፡ ሃሌሉያ ለአብ፣ ሃሌሉያ ለወልድ፣ ሃሌሉያ ለመንፈስ ቅዱስ፣ ቅዱስ እግዚአብሔር፣ ቅዱስ ኃያል፣ ቅዱስ ሕያው የማይሞት›› እያልን እንሰግዳለን::


ሥርዓተ አምልኮ  ክፍል ሦስት

ሥርዓተ ክብረ በዓላት

በዓላት ከማንኛውም ቀናት የበለጠ አምላካችን እግዚአብሔርን የምናመሰገንባቸውና የምናወድስባቸው፣ የተቀደሱትን ዕለታት በማሰብና በመዘከር በዝማሬ፣ በሽብሻቦና በእልልታ የምናከብርባቸው ናቸው፡፡ ታቦታት ከመንበረ ክብራቸው የሚወጡባቸውና ሕዝበ ክርስቲያኑን የሚባርኩባቸው ስለሆኑም በክብርና በድምቀት ይከበራሉ፡፡   

በዓል

በዓል አብዐለ፣አከበረ›› ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ነው፡፡ የቃሉ ትርጕም ደግሞ ‹‹መታሰቢያ ማድረግ፣ ማክበር፣ ማሰብ፣ መዘከር፣ ማስታወስ›› ማለት ነው፡፡ ከዚህም ባሻገር በዓል በቁሙ ‹‹የደስታ እንዲሁም የዕረፍት ቀን እንደሆነ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌም በመዝገበ ቃላታቸው ላይ ገልጸዋል፡፡ (ገጽ ፪፸፱)

በቤተ ክርስቲያን አስተምህሮና በምእመናን ዘንድ የተለመደው አስተሳስብና አመለካከት ደግሞ በዓል “በዓመትና በወር የሚከበር፣ ያለፈ ነገር የሚታሰብበት፣ ሕዝብ የበዓሉን ምሥጢር እያሰበ ደስ ብሎት እና በአማረ ነጭ ልብስ አጊጦ የሚዘምርበት፣ እልል የሚልበት፣ ሽብሸባና ጭብጨባ የሚያደርግበት (የሚያበዛበት) ቀን››  ነው፡፡

ሥርዓተ አምልኮ

ክፍል ሦስት

ጥር ፰፤፳፻፲፭ ዓመተ ምሕረት

ሥርዓተ ክብረ በዓላት

በዓላት ከማንኛውም ቀናት የበለጠ አምላካችን እግዚአብሔርን የምናመሰገንባቸውና የምናወድስባቸው፣ የተቀደሱትን ዕለታት በማሰብና በመዘከር በዝማሬ፣ በሽብሻቦና በእልልታ የምናከብርባቸው ናቸው፡፡ ታቦታት ከመንበረ ክብራቸው የሚወጡባቸውና ሕዝበ ክርስቲያኑን የሚባርኩባቸው ስለሆኑም በክብርና በድምቀት ይከበራሉ፡፡   

በዓል

በዓል አብዐለ፣አከበረ›› ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ነው፡፡ የቃሉ ትርጕም ደግሞ ‹‹መታሰቢያ ማድረግ፣ ማክበር፣ ማሰብ፣ መዘከር፣ ማስታወስ›› ማለት ነው፡፡ ከዚህም ባሻገር በዓል በቁሙ ‹‹የደስታ እንዲሁም የዕረፍት ቀን እንደሆነ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌም በመዝገበ ቃላታቸው ላይ ገልጸዋል፡፡ (ገጽ ፪፸፱)

በቤተ ክርስቲያን አስተምህሮና በምእመናን ዘንድ የተለመደው አስተሳስብና አመለካከት ደግሞ በዓል “በዓመትና በወር የሚከበር፣ ያለፈ ነገር የሚታሰብበት፣ ሕዝብ የበዓሉን ምሥጢር እያሰበ ደስ ብሎት እና በአማረ ነጭ ልብስ አጊጦ የሚዘምርበት፣ እልል የሚልበት፣ ሽብሸባና ጭብጨባ የሚያደርግበት (የሚያበዛበት) ቀን››  ነው፡፡

የበዓላት ዓይነት

በቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ በዓላት ሁለት ዓይነት ናቸው፡፡ በቤተ ክርስቲያን የሚከበሩ እና በዐደባባይ የሚከበሩ በዓላት ተብለውም ይጠራሉ፡፡

በቤተ ክርስቲያን የሚከበሩ በዓላት

ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በየወሩም ሆነ በየዓመቱ በቀዳሚነት በአምላካችን ስም የሚታሰቡ በዓላትን ማለትም ‹‹በአጋዝእተ ዓለም ሥላሴ፣ በቅዱስ አማኑኤል፣ በጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ››  እና በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስም ማለትም ‹‹ልደታ ለማርያም፣ በዓታ ለማርያም፣ ኪዳነ ምሕረት፣ ብዙኃኗ ማርያም፣ በዓለ አስተርእዩ ለማርያም እና ፍልሠታ ለማርያምን›› ታከብራለች፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ የሊቃነ መላእክትን፣ የቅዱሳንን፣ የጻድቃንና የሰማዕታትን የመታሰቢያ በዓል ታከብራለች፡፡

በቤተ ክርስቲያን የሚከበሩ ዓመታዊ በዓላት አከባበር ሥርዓት ከዋዜማ ጀምሮ እስከ ዕለቱ ሠርክ ጉባኤ ድረስ ይዘልቃል፤ በቅዱስ ያሬድ ዝማሬ ማኅሌተ ጽጌ ታጅቦ የሚከበረው የበዓሉ ዋዜማ ከምሽት ጀምሮ በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ማኅሌትና በምእመናን እልልታና ጭብጨባ ደምቆ ያድራል፡፡

ከጸሎተ ኪዳንና ቅዳሴ በኋላም ታቦተ ክብሩ ከመንበሩ ወርዶ በቤተ ክርስቲያን የተሰበሰበውን ሕዝብ ለመባረክ ዑደት በሚያደርግበት ጊዜ የደብሩ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ዕለቱን በተመለከተ የተማሯቸውንና ያጠኗቸውን መዝሙራት በቅደም ተከተል ያቀርባሉ፡፡ ታቦቱም ሦስት ጊዜ ዑደት አድርጎ በዐውደ ምሕረቱ ሲቆም ሊቃውንቱ እንዲሁም የአባቶቻቸውን ፈለግ በመከተል የሰንበት ተማሪዎች ወረብ ያቀርባሉ፡፡

በመቀጠል ደግሞ ለክብረ በዓሉ የተመረጡ ብቁ መምህራን ለዕለቱ በሚመጥን መልኩ ቃለ እግዚአብሔርን ካስተማሩ በኋላ በሰዎች ዘንድ የሚደረጉ ምስክሮችና ሥዕለቶች በዐውደ ምሕረቱ ይነገራሉ፡፡ አልፎ አልፎም ከቤተ ክርስቲያን ልማት ጋር የተያያዙ ሥራዎች፣ ርእሰ ጉዳዮች፣ ገለጻዎች እንዲሁም በምእመኑ የሚደረጉ መዋጮዎች ይከናወናሉ፡፡

የደብሩ አስተዳዳሪ የሆኑ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ቃለ ምዕዳን ከሰጡ በኋላም ታቦተ ክብሩ በዝመሬ፣ በእልልታና በጭብጨባ ታጅቦ ወደ መንበረ ክብሩ ይመለሳል፡፡ ሕዝቡም የቀረውን ጊዜ በተገቢው መንገድ ለማክበርና ለመዘከር ወደ ቤቱ ይሄዳል፡፡ ለበዓል ባዘጋጁት መዐድም ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲሁም ከነዳያን ጋር በማቋደስ ያከብራሉ፡፡

ከዚያም ተመልሰው በሠርክ ጉባኤ ጸሎት ካደረሱ በኋላ ለዕለቱ ከሚመደቡ ዘማርያን ጋር በመሆን በዓሉን ያከብራሉ፡፡ በተጋባዥ መምህራንም ከቀኑ የቀጠለ ትምህርት በመማር እስከ ምሽት ድረስ ከካህናቱ ጋር ይቆያሉ፡፡ በመጨረሻም በዓሉን አባቶች በጸሎት ያሳርጉታል፡፡

የዐደባባይ በዓላት አከባበር

በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት አስተምህሮ መሠረት የዐደባባይ በዓላት ሁለት ናቸው፡፡ እነርሱም የመስቀልና የጥምቀት በዓላት ናቸው፡፡ እነዚህም የጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ግማደ መስቀል በቅድስት ዕሌኒ መጋቢት ፲ ከመገኘቱ በፊት መስከረም ፲፯ ቁፋሮ ያስጀመረችበት  እና መስከረም ፲፮ ለመስቀሉ ቤተ መቅደስ የሠራችለት ቀን እንዲሁም ጌታችን ኢየሱስ በመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ እጅ በጥር ፲፩ የተጠመቀበት ቀን ታቦተ ክብሩ ከመንበሩ ወርዶና ከየአጥቢያ ቤተ ክርስቲያኑ በሚወጡ ካህናትና አገልጋዮች ታጅቦ ወደ መስቀል ዐደባባይ እንዲሁም ወደ ባሕረ ጥምቀቱ ስፍራ የሚወርድበት ሂደት በመሆኑ እነዚህ ሁለት በዓላት የሚከበሩት በዐዳባባይ ነው፡፡ በመቀጠልም የበዓላቱን አከባበር ነጣጥለን በአጭሩ እንመለከታለን፡፡

 የመስቀል በዓል አከባበር   

በሀገራችን ኢትዮጵያ የመስቀልን በዓል የምናከብረው ከመስከርም ፲፮ ቀን ደመራ በመደመርና ችቦ በማብራት ነው፡፡ ይህም ንግሥት ዕሌኒ መስቀሉን ለማግኘት ፍለጋ ስትሰማራ ያደረገችውን ክንውን የሚያወሳና የሚዘክር ነው፡፡

በመስከረም ፲፯ ቀን ደግሞ በተለይም መስቀሉ የተገኘበትን ቀን በማውሳት ሌሊቱን በማኅሌተ  ጽጌ ዝማሬ ነግህኑን በጸሎተ ኪዳንና በቅዳሴ እንዲሁም ዕለቱን ደግሞ ታቦቱን በማጀብ በዓሉ ተከብሮ ይውላል::

በየዓመቱ በመስቀል ዐደባባይ በመገኘት በዓሉን በሽዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በመስቀል ዐደባባይ ተግኝተው ያከብራሉ፡፡ በዚህም ሥርዓት ውስጥ ጌታችን አምላካችን  መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ ያደረገልንን ሁሉ በማሰብና ቀኑንን በመዘከር እርሱን እያመሰገንን እንውላለን፡፡ ሆኖም ግን በቅርብ ጊዜ በመስቀል ዐደባባይ መከበር ከጀመረ ዘመናት ያስቆጠረውን የመስቀል በዓል ‹‹እኛም አንድ ሃይማኖታዊ ሁነት ፈጥረን ማክበር አለብን›› በሚል ሰበብ በእስልምና ሃይማኖት ታሪክ ውስጥ የሌለ ‹‹የዐደባባይ አፍጥር መርሐ ግብርን›› ምክንያት አድርጎ ቦታውን ዒላማ በማድረግ በመነሣት ክብረ በዓሉ እንዳይከበር ለማገት የተሞከረ ቢሆንም አለመግባባቶች ተፈትተውና ችግሮቹ ተቀርፈው የመስቀል በዓል እንደ ቀድሞ መከበር ቀጥሏል፡፡

ከዚህም ባሻገር ምእመናን በየአጥቢያ ቤተ ክርስቲያናቸውም በመገኘት የመስቀል በዓልን ደመራ በመለኮስ፣ ችቦ በማብራትና ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንን በማጀብ ያከብራሉ፡፡

የጥምቀት በዓል አከባበር

የጥምቀት በዓል በሀገራችን የሚከበረው ከዋዜማው ከከተራ ጀምሮ ታቦታቱ ከየአብያተ ክርስቲያናቱ በክብር ወጥተው በሕዝቡ እልልታ፣ ሽብሽባ እና በካህናቱ ያሬዳዊ ዜማ ወደ ወንዝ አልያም ወደተዘጋጀ የውኃ ቦታ በመውረድ ሕዝቡን በሰፊው የሚያሳተፍበት የጥምቀት ሥነ ሥርዓቱን በማከናወን ነው።

በዓሉ በተለይ በጎንደር ከተማ በድምቀት ይከበራል፡፡ የበርካታ ታቦታት መገኛ የሆነችው ከተማዋ ሕዝቡን ለማጥመቅ የምትጠመቅበት የቅዱስ ፋሲለደስ ቤተ ክርስቲያን ያለበት የሚዋኝበት የጥምቀት ስፍራ ነው፡፡ በባሕረ ጥምቀቱ አካባቢ መቀመጫ መድረክ እንዲሁም እስከ ፶ ሜትር የሚረጭ የውኃ ማስተላለፍያም በማዘጋጀት በጥር ፲፩ ቀን ሊቀ ጳጳሳቱ ሕዝበ ክርስቲያኑን ያጠምቃሉ!

ከበዓሉ ረድኤት ያሳትፈን፤ አሜን!


ሥርዓተ አምልኮ-ክፍል ዐራት

ንዋያተ ቅድሳት

 

የቤተ ክርስቲያናችን ታላቁ ሊቅ ኪዳኔ ወልድ ክፍሌ የቃሉን ትርጉም በመጽሐፋቸው እንዲህ ብለው አስቀምጠውታል፤ “ንዋየ ማለት “ገንዘብ፣ ጥሪት፣ ቅርስ፣ ወርቅ፣ ብር፣ ከብት” ነው፡፡ (መጽሐፈ ሰዋሰው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ፣ ገጽ ፮፻፴፪) ቅዱሳት ማለት ደግሞ “ቅድስና፣ ክብር፣ ንጽሕና፣ ጸጋ” ነው፡፡ (ገጽ ፯፻፹፬)

ንዋያተ ቅዱሳት የቤተ ክርስቲያን መገልገያዎች ናቸው፤ አገልግሎታቸውም እንደ ዓይነታቸውና እንደ ስያሜያቸው ይለያያል፡፡ ስለዚህም በቅደም ተከተል እንመለከታቸዋል፡፡

 

አምላካችን እግዚአብሔር ዓለምን ሲፈጥር ፍጥረት ሁሉ እንዲያመልከውና እንዲመሰግነው ነው፤ በአርአያውና በአምሳሉ የተፈጠርን ሰዎች ብቻም ሳይሆን በደመ ነፍስ የሚንቀሳቀሱ እንስሳት ሳይቀር ፈጣሪያቸውን ያመሰግናሉ፡፡ በተለይም በክርስቶስ ክርስቲያን ለተባልን ሰዎች የምናመልክበት የቅድስና ሕይወት ሰጥኖናል፡፡ ሕጉን ጠብቀን በሥርዓቱ ለምንኖር ለእኛ እርሱ ምሕረቱ የበዛ በመሆኑ በሕይወታችን ውስጥ ሊኖር ይወዳል፤ በቤቱም ስንገኝ ደስ ይሰኛል፡፡ እርሱን በዓይን ለማየት ባይቻለንም መኖሩን የምናውቀበትና የምናመሰግንበት፣ ለእርሱም የአምልኮት ስግደት የምናቀርብበትና የምናዜምበት በአጠቃላይ የምናመልክበት መንገድ ፈጥሮልናል፡፡ ለዚህም የከበረ ተግባር መፈጸሚያ ባርኮና ቀድሶ ንዋያተ ቅድሳትን ሰጥቶናል፡፡

 

ንዋያተ ቅድሳት

 

የቤተ ክርስቲያናችን ታላቁ ሊቅ ኪዳኔ ወልድ ክፍሌ የቃሉን ትርጉም በመጽሐፋቸው እንዲህ ብለው አስቀምጠውታል፤ “ንዋየ ማለት “ገንዘብ፣ ጥሪት፣ ቅርስ፣ ወርቅ፣ ብር፣ ከብት” ነው፡፡ (መጽሐፈ ሰዋሰው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ፣ ገጽ ፮፻፴፪) ቅዱሳት ማለት ደግሞ “ቅድስና፣ ክብር፣ ንጽሕና፣ ጸጋ” ነው፡፡ (ገጽ ፯፻፹፬)

ንዋያተ ቅዱሳት የቤተ ክርስቲያን መገልገያዎች ናቸው፤ አገልግሎታቸውም እንደ ዓይነታቸውና እንደ ስያሜያቸው ይለያያል፡፡ ስለዚህም በቅደም ተከተል እንመለከታቸዋል፡፡

 

፩. ታቦት፡- የልዑል እግዚአብሔር ማደሪያ ነው፡፡ በኦሪት ዘፀአት ተመዝግቦ እንደምናገኘው አምላካችን እግዚአብሔር ነቢዩ ሙሴን ታቦቱን ከግራር፣ ከእንጨትና ከወርቅ እንዲሠራ ባዘዘው መሠረት ሠርቶታል፡፡ (ዘፀ.፳፭፥፩-፳፪፣፵፣፳) ርዝመቱንና ቁመቱንና መጥኖ እንደሠራው መጽሐፍ ቅዱስ ይገልጻል፡፡

 

ጽላት “ሰሌዳ ወይም መጸለያ” ማለት ነው፤ የመጀመሪያዋ ጽላት በግብር አምላካዊ የተገኘች ሁለት ክፍሎች ያሏትና ዐሥሩ ትእዛዛት የተጻፈባት እንዲሁም ነቢዩ ሙሴ በደብረ ሲና ከአምላካችን የተቀበላት በኋላም እስራኤል ለጣዖት ሲሰግዱ አይቶ ቢደነግጥ ከእጁ ወድቃ የተሰበረችው የዕንቁ ጽላት ናት፡፡ (ዘፀ.፴፣፲፭-፳)

ሁለተኛዋ ጽላት ደግሞ ነቢዩ ሙሴ በፊተኛዋ አምሳል መሠረት በግብር አምላካዊ ዐሥሩ ትእዛዛት የተጻፈባት በቤተ መቅደስ በታቦቱ ላይ ሆና ብዙ ተአምር ያደረገች ናት፡፡ (ዘፀ. ፴፬፥፩-፳፰) “ታቦተ ጽዮን” ብለን የምንጠራት ዐሥርቱ ቃላት የተጻፈባት ጽላትና በንጉሥ ሰሎሞን ዘመን ወደ ሀገራችን ኢትዮጵያ፣ በአክሱም ከተማ፣ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በክብር ተቀምጣ ትገኛለች፡፡ በእርግጥ ከተቀመጠችበት ቤተ መቅደስ ስለማትወጣ ማንም መግባትም ሆነ ታቦቱን ማየት አይችልም፡፡ ሆኖም ግን ታቦቷ ወደ ሀገራችን በገባችበት ዕለት በኅዳር ፳፩ ምእመናን ከየክፍለ ሀገራቱ ወደ ቤተ ክርስቲያን በመምጣት ለታቦተ ክብሩ ይሰግዳሉ፡፡ አምላካቸውንም ያመሰግናሉ፡፡

 

ይህ ብቻም አይደልም፤ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ታቦተ ጽዮንን ምሳሌ በማድረግ በክፍለ ሀገራቱ ለሚገኙ ምእመናን አምልኮተ እግዚአብሔርን ይፈጽሙ ዘንድ ታቦታትን ቀርጻ በክብር ቤተ መቅደስ ውስጥ ታስቀምጣለች፡፡ በእርግጥ የሚሠሩት በወርቅ የተሠሩ ባይሆኑና መጠናቸውና ስፋታቸውም ባይተካከልም በአምልካችን እግዚአብሔር፣ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን፣ በመላእክት፣ በቅዱሳን፣ በሰማዕታት ዓመታዊ ክብረ በዓላት ላይ ይከበራሉ፤ ይሰገድላቸዋል፤ ይዘመርላቸዋልም፡፡

 

፪. መንበር፡– የታቦት ማስቀመጫ መንበር ነው፤ የሚገኘውም በቤተ መቅደስ በክብር ታቡቱን ይዞ ነው፡፡ ከወርቅ፣ ከብር፣ ከብረት ወይም ከእንጨት ይሠራል፡፡ መንበሩን ከማስቀመጥ በተጨማሪም ጸሎት ይጸለይበታል፤ መሠዋዕት ይሠዋበታል፤ በመንበሩ ላይ በመደበኛነት የሚቀመጡ ንዋያተ ቅድሳት ታቦት /ጽላትና/ ሥዕለ ማርያም፣ ምስለ ፍቁር ወልዳ ሲሆኑ በቅዳሴ ጊዜ ሥጋውን ደሙን ለመፈተት የምንገለገልባቸው ጻሕል፣ ጽዋዕ፣ ማኀፈዳት፣ ዕረፈ መስቀል፣ መስቀል፣ ዕጣን ይቀመጡበታል፡፡

 

ከቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ቀሳውስቱ ውጪ መንበሩን የሚዳስስና የሚገለገልበት የለም፡፡ ዲያቆናት ግን ከበውት መቆም ይችላሉ፡፡ መንበር የታቦት፣ የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፣ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፣ የመንበረ ጸባዖት፣ ልዑካን የሠራዊተ መላእክት ምሳሌ ነው፡፡

 

፫. አትሮንስ፡- ቀሳውስትም የሚጸልይበቱና መጽሐፈ ቅዳሴ የሚያስቀምጡበት ነው፡፡ አትሮንስ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዙፋን፣ መጽሐፍ፣ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም መጽሐፍ ምሳሌ ነው፡፡

 

፬. ቅዱሳት ሥዕላት

ቅዱሳት ሥዕላት የአንድን ቅዱስ ምስል የሚገልጹ፣ ገድላቸውና ተአምራቸውን የሚገልጹ በመሆናቸው ይሰገድላቸዋል፤ ይህም የጸጋ ስግደት ነው፡፡ ሆኖም ግን ለእግዚአብሔር አምላክ ቅዱስ ሥዕል የሚደረግ ስግድት የአምልኮት ስግደት ነው፡፡ ስለዚህም በቤተ ክርስቲያንም ሆነ በሌሎች ቅዱሳት ስፍራ የአምላካችን ሥዕላት ፊት ቆመን ለእርሱ በመስገድና በፍጹም ትሕትና መማጸን፣ ማመስገንና ማምለክ ተገቢ ነው፡፡

 

፭. አልባሰ ቅዳሴ፡- ካህናት ሥጋ ወደሙን በሚፈቱቱ ጊዜ የሚለብሱት ነጭና የአገልግሎት ልብስ በመሆኑ ከንዋያተ ቅድሳት መካከል ይመደባል፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ነቢዩ ሙሴን ባዘዘው መሠረት አሮን ይለብሰው የነበረው ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊና ከቀይ ግምጃ የተሠራና ዐሥራ ሁለት የወርቅ ሻኩራዎች ያሉት ልብስ ነው፡፡ (ዘፀ.፴፱፥፩-፳፭) እርሱም አልባሰ ቅዳሴ ለብሶ ወደ መቅደስ በገባ ጊዜ ከሻኩራዎች ድምፅ ይሰማ ስለነበር በድምፁም ምክንያት ሕዝቡ ከያዛቸው በሽታ ይፈወሱ ነበር፡፡ (ዘፀ.፳፰፥፴፭)

 

፮. አክሊል፡- በዘመነ ኦሪት ካህናት አክሊል ያደርጉ ነበር፤ ይህም ከጥሩ ወርቅ የተሠራና “ቅድስና ለእግዚአብሔር” የሚል ቃል የተጻፈበት ማዕተብ ያለው የተቀደሰ ነው፡፡ (ዘፀ. ፴፱፥፴) በሐዲስ ኪዳን ሥርዓትም በቅዳሴ ጊዜ ካህናቱ አክሊል ማድረጋቸው ይህን መሠረት ያደረገ ነው፡፡ ነገር ግን በአክሊሉ ላይ የሚቀረጸው መስቀል ነው፡፡ የክብር ምልክት ስለሆነም ለሥጋና ደሙ ክብርም አክሊል ይደፋሉ፡፡ (፩ኛቆሮ.፱፥፳፭)

 

፰. ዕጣን፡– በቅዳሴ ሰዓት እንዲሁም በሌሎች መንፈሳዊ አገልግሎቶች ጊዜ የሚቀርብ መባዕ ነው፤ መዓዛው እጅግ ደስ የሚል ነው፤ ንጹሕና ነውር የሌለበትም ሊሆን ይገባል፡፡ (ዘፀ.፴፥፴፭) “ለእግዚአብሔር የተመረጠውን መልካም ዕጣን ከመቅደስ ውጪ ለግል መጠቀም አልተፈቀደም” እንዲል፡፡ (ዘፀ.፴፥፴፯-፴፰)

 

፱. ጽንሓሕ፡– የዕጣን ማጠኛ ማሻታቻ ጽንሓሕ ይባላል፡፡ የሚሠራውም ከብረት ወይም ከናስ ወይም የወርቅና የብር መልክ ካላቸው እንዲሁም እሳት በቀላሉ ከማይጐዳቸው ማዕድናት ነው፡፡

ይህም ቤተ ክርስቲያናችንና ካህናቱ በጸሎተ ኪዳን፣ በማኅሌተ ጽጌ እና በቅዳሴ ጊዜ በቤተ መቅደሱና በቅጽረ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በመመላለስ ለዕጣን ለማጠኛ ይጠቀሙበታል፡፡ የኦሪት ጽንሓሕ -ሸምሸር ሸጠን ከሚባል ከማይነቅዝ እንጨት የተቀረጸና በወርቅ የተለበጠ ያለው ነበር፡፡ (ዘሌ.፲፮፥፲፪፣ ዕብ.፱፥፬) በሐዲስ ኪዳን ግን ከንጹሕ ወርቅ ማዘጋጀት አይችልምና ከላይ በተገለጸው መሠረት ተሠርቶ ለአገልግሎት ይውላል፡፡

 

፲. መጻሕፍት፡- ቅዱሳት መጻሕፍት የእግዚአብሔር ቅዱሳ ቃል የተጻፈባቸው የተቀደሱ መጻሕፍት ናቸው፡፡ በቤተ ክርስቲያን ሥርዓትም በርካታ ጥቅም አላቸው፡፡ ሆኖም ግን ለአምልኮት የምንጠቀምባቸው ጊዜ ማለት በጸሎተ ኪዳንና በቅዳሴ ጊዜ ወንጌል የሚነበብት መጽሐፍ ቅዱስና የምስባክ መዝሙር የሚገኝበት መጽሐፈ ግጻዌ ናቸው፡፡ መጽሐፈ ጸሎተ ዕጣን ተጠቃሽ ነው፡፡

 

፲፩. መስቀል፡-ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት መስቀል የክርስትናችን ማኅተም በመሆኑ በቤተ መቅደስም ሆነ በቅዱሳት ስፍራ ተምሳሌቱ የተገለጸ ነው፡፡ በዚህም መሠረት በቅዳሴ ጊዜ ካህናቱ የእጅ መስቀል ዲያቆናት ደግሞ ባለመጾር መስቀል ይይዛሉ፡፡ ይህም ምሳሌነቱ ጌታችን በዕለተ ዓርብ መስቀሉን ተሸክሞ እየወደቀ አየተነሣ ቀራንዮ የመውጣቱ ነው፡፡

 

ስለዚህም በመስቀል ላይ ተሠውቶ ፍቅሩን ለገለጸልን ለጌታችን ውለታ ምስጋናና ክብር ይገባልና በፍጹም ትሕትናና ክብር እንሰግድለታለን፤ እናመሰግነዋለንም፡፡ በዘወትር ጸሎታችንም “ዓለምን ሁሉ ለማዳን ሲል ኢየሱስ ክርስቶስ ለተሰቀለበት መስቀልም እሰግዳለሁ” በማለት እንሰግዳለን፡፡

 

፲፪. መሶበ ወርቅ፡- መሥዋዕት ማክበሪያ ነው፤ ዲያቆን በራሱ ተሸክሞ መሥዋዕቱን ከቤተልሄም ወደ መቅደሱ ያቀርብበታል፡፡ ይህም ተምሳሌቱ ከቤተልሔም ወደ መቅደስ መምጣቱና ጌታ ነቢያት በተናገሩለት ትንቢት መሠረት በቤተልሐም ተወልዶ በቀራኒዮ የመሠዋቱ ምሳሌ ነው፡፡

 

፲፫. ጻሕል፡- ይህ ጐድጐድ ያለ ወጭት ሲሆን ከሸክላ ወይም ከናስ ከብረት ወይም ከወርቅ ከብር የሚሠራ ነው፡፡ በኦሪት ዘመን ኅብስተ ገጽ ይቀርብበት ቢሆንም በሐዲስ ኪዳን ግን ከመንበሩ ላይ ሆኖ የጌታችን ሥጋ ይቀመጥበታል፤ ምሳሌነቱም የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መቃብር ነው፡፡

 

፲፬. ጽዋዕ፡– ኩባያ፣ ዋንጫ፣ የመጠጥ መሣሪያ፣ የሸክላ፣ ከእንጨት፣ ከቀርን፣ ከማዕድን የሚሠራ ነው፡፡ የደሙ ማቅረቢያ ሲሆን የጌታችን መቃብር መላእክት ከጌታችን ጐን የፈሰሰውን ደም ተቀብለው በዓለም ሁሉ የረጩበት የብርሃን ጽዋ ምሳሌም ነው፡፡

 

፲፭. ማኀፈድ፡– ከተመረጠ ጨርቅ የሚሠራ የሥጋውና የደሙ መሸፈኛ ሲሆን አምስት ማኅፈዳት አገልግሎት ይሰጥባቸዋል፤ አንድ ጻሕሉ ላይ ይነጠፋል፤ ሦስቱ ኀብስተ ቁርባኑ ይሸፈንባቸዋል፤ አንዱ የጽዋዕ መሸፈኛ ነው፡፡ የጌታችን ሰበን ምሳሌ ነው፡፡

 

፲፮. ተቅዋም፤ መቅረዝ፡– የመብራት መስቀያ ወይም ማስቀመጫ ነው፤ ከኦሪት ዘመን ጀምሮ እንደነበረው ሥርዓት መቅረዝ የሚሠራው ከማይነቅዝ እንጨት የተቀረጸ፣ በወርቅ የተለበጠ፣ እንደ ጽዋዕ እግርና ሰባት ቅርንጫፎች ያሉት ነው፤ አገልግሎቱም ተመሳሳይ ነው፡፡ በመካከለኛ የተቀዳው ዘይት በስድስቱ