ቅድስት ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን፡ እግዚአብሔር ልባቸውን ባነሳሳቸው ጥቂት ምዕመናን፡ በአውሮፕያውያን ቀን አቆጣጠር ጃንዋሪ 17, 1999 (January 17, 1999) ተመሰረተ።ለዚህም መነሻው: እንደ አጋጣሚ ሆኖ የ1998 የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አመታዊ ፒክኒክ: የፍልሰታ ጾም ፊቺ ጋር ስለተገጣጠመና: በአንዳንድ እናቶች: አገራችን ብንሆን ኖሮ ዛሬ አስቀድሰን ጾም እንፈታ ነበር ሲሉ: ሌሎችም ታዲያ ለምን እዚህ ቤተክርስቲያን አይኖረንም? የሚለው የተቀደሰ ሀሳብ ስለመጣላቸው: በተለያየ ጊዜና አካባቢ እየተገናኙ ሲወያዩ ቆይተው: የካቲተ 17, 1999 ላይ በነበረው ምልዐተ ጉባኤው ላይ: ለውይይት የቀረበውን ረቂቅ መተዳደሪያ ደንብና ኮድ ኦፍ ኤቲክስ አጽድቆ: ስሙንም ኪደነምህረት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ብሎ: ቀጥሎም የሚመሩትን የቦርድ አባላት መርጦ በደስታ ተበተነ።
ዓመታዊ ንግስ በሮቸስተር ኪዳነምህረት
የኢ .ኦ. ተ ቤተክርስቲያን
ከግብጽ ቤተ ክርስቲያን ጋር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አመራር ላይ ብዙ ጊዜ የወሰደ ድርድር ከተደረገ በኋላ ስምምነት ተደርጎ፥ እሑድ፣ ሰኔ ፩ ቀን ፲፱፻፶፩ ዓ/ም፤ ንጉሠ ነገሥቱም በተገኙበት ሥነ-ሥርዓት ፓፓው አቡነ ቄርሎስ ፮ኛ በብፁዕ አቡነ ባስልዮስ ላይ የሢመቱን ሥርዓተ-ጸሎት አድርሰው፤ የፓትርያርክነቱን ዘውድ ባርከው ደፉላቸው። ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ አቡነ ባስልዮስ በግብጽ ፓትርያርክ እጅ በዚህ ማዕርግ ሲቀቡ የመጀመሪያውም የመጨረሻውም ኢትዮጵያዊ መሆናቸው ነው።
ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት
ዘኢትዮጵያ አቡነ ቴዌፍሎስ
፲፱፻፷፫ - ፲፱፻፷፰
ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት
ዘኢትዮጵያ አቡነ ተክለሃይማኖት
፲፱፻፷፰ -፲፱፻፹