ሥርዓተ አምልኮ ክፍል አንድ

ርዓት  “ሠርዐ” ሠራ ከሚለው የግእዝ ቃል የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ደንብ፣ አሠራር፣ መርሐ ግብር ማለት ነው። በሃይማኖት ውስጥ የሚፈጸም የመንፈሳዊ አገልግሎትና አሠራር እንዲሁም ክርስቲያናዊ ሥርዓትን ያመለክታል።

 ሥርዓተ አምልኮት

የቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ አምልኮት ለአምላካችን እግዚአብሔር የሚቀርብ ሥርዓት ነው፡፡ ይህም ሥርዓተ ጸሎትን፣ ሥርዓተ ጾምን፣ ሥርዓተ ምጽዋት፣ ሥርዓተ ስግደትን፣ ሥርዓተ በዓላትን፣ ሥዕላትን፣ መስቀልንና ንዋያተ ቅድሳትን ያካትታል